ሕዝቅያስም በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቅያስ ዘመን ቍጣውን አላመጣባቸውም።
ያዕቆብ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል፤” ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ጸጋን አብዝቶ ይሰጠናል፤ መጽሐፍም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” ያለው ስለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” እንደሚል፥ የሚሰጠው ጸጋ ግን ከሁሉም ይበልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም መጽሐፍ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑቶች ግን ጸጋን ይሰጣል” ስለሚል እግዚአብሔር የሚሰጠው ጸጋ ከሁሉም ይበልጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል። |
ሕዝቅያስም በኢየሩሳሌም ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፤ እግዚአብሔርም በሕዝቅያስ ዘመን ቍጣውን አላመጣባቸውም።
አሁንም አቤቱ፥ የጻድቃን አምላካቸው አንተ ነህ። ንስሓን የፈጠርህ ለጻድቅ ሰው አይደለምና፥ አንተን ላልበደሉ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም አይደለምና፤ ነገር ግን የእኔን የኃጥኡን ንስሓ ወደ ማየት ተመለስ።
በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራ በሚኖሩበት ላይ ቃሌን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ይከብራልና።”
እንዲሁም ጐበዞች ሆይ! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ልበሱ፤ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል።
አትመኩ፤ የኵራት ነገሮችንም አትናገሩ፤ ፅኑዕ ነገርም ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ዙፋኑን ያዘጋጃል።