እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “በእውነት ወንድማችንን በድለናል፤ እኛን በመማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና፤ ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።”
ያዕቆብ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታል፤ ምሕረት በፍርድ ላይ ያይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታልና፤ ምሕረትም ፍርድን ያሸንፋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ፍርድ ምሕረት ለማያደርግ ሰው ምሕረት አያደርግም፤ ሆኖም ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሕረትን ለማያደርግ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይሆናልና፤ ምሕረትም በፍርድ ላይ ይመካል። |
እነርሱም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፥ “በእውነት ወንድማችንን በድለናል፤ እኛን በመማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና፤ ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።”
አሁንም ስሙ፤ የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችሁ ነድዶአልና ከወንድሞቻችሁ የወሰዳችኋቸውን ምርኮኞች መልሱ።”
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ነገር ግን የሚመካው፦ ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግዚአብሔር።
እኔ ሕያው ነኝና ኀጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኀጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! ተመለሱ፤ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።
በደልን ይቅር የሚል፥ የርስቱንም ቅሬታ ዓመፅ የሚያሳልፍ እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረትን ይወድዳልና ቍጣውን ለዘላለም አይጠብቅም።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።
ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።