ያዕቆብ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! አትሳቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ አትታለሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! አትታለሉ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! አትታለሉ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ አትሳቱ። |
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ዘወትር እንደምትሰሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፥ ሳልኖርም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ ሆናችሁ ለድኅነታችሁ ሥሩ።
አሁንም የተወደዳችሁና የምናፍቃችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ደስታችንና አክሊላችን ናችሁ፤ ወዳጆቻችን ሆይ፥ እንዲህ ቁሙ፤ በጌታችንም ጽኑ።
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለ ጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
ወንድሞች ሆይ! እርስ በርሳችሁ አትተማሙ። ወንድሙን የሚያማ በወንድሙም የሚፈርድ ሕግን ያማል፤ በሕግም ይፈርዳል፤ በሕግም ብትፈርድ ፈራጅ ነህ እንጂ ሕግን አድራጊ አይደለህም።
ከሁሉም በፊት ወንድሞቼ ሆይ! በሰማይም ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፤ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።