La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 7:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሚ​ታ​ረ​ሰ​ውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍር​ሀት ይመ​ጣል፤ የበ​ጎች መሰ​ማ​ርያ ይሆ​ናል፤ በሬ​ዎ​ችም ይረ​ግ​ጡ​ታል፤ እሾ​ህና ኵር​ን​ች​ትም ያጠ​ፋ​ዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኵርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደ ነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብቶች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኩርርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብታዎች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀድሞ በዶማ ተቈፍረው እህል ይበቅልባቸው የነበሩ ኰረብቶች ሁሉ ኲርንችትንና እሾኽን በመፍራት ማንም ወደዚያ አይሄድም፤ ነገር ግን የከብትና የበግ መንጋ መሰማሪያ ብቻ ይሆናሉ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተንሣ ወደዚያ አትሄድም፥ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 7:25
8 Referencias Cruzadas  

ለዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ለመ​ንጋ ማሰ​ማ​ር​ያም ትሆ​ና​ለች፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዳ​ቸ​ውም የለም።


የተ​ማ​ረኩ እንደ በሬ​ዎች ይሰ​ማ​ራሉ፤ የተ​ረ​ሱ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሲፈ​ልጉ እንደ በግ ጠቦ​ቶች በማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ይሰ​ማ​ራሉ።


ይመ​ጡ​ማል፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ በሸ​ለቆ፥ በመ​ን​ደ​ሮች፥ በም​ድር ጕድ​ጓድ፥ በድ​ን​ጋ​ይም ዋሻ ውስጥ በጫካ ሁሉ ላይ ይሰ​ፍ​ራሉ።


በፍ​ላ​ጻና በቀ​ስት ይገ​ቡ​ባ​ታል፤ ምድ​ሪቱ ሁሉ ትጠ​ፋ​ለ​ችና፥ እሾ​ህ​ንና ኵር​ን​ች​ት​ንም ትሞ​ላ​ለ​ችና።


እስ​ራ​ኤል እን​ደ​ም​ት​ደ​ነ​ብር ጊደር ደን​ብ​ሮ​አል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ፊው ቦታ እንደ ጠቦት ያሰ​ማ​ራ​ዋል።


ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል።