ኢሳይያስ 7:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍላጻና በቀስት ይገቡባታል፤ ምድሪቱ ሁሉ ትጠፋለችና፥ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለችና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ በኵርንችትና በእሾኽ ስለምትሸፈን፣ ሰዎች ወደዚያ የሚገቡት ቀስትና ፍላጻ ይዘው ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱ በኩርንችትና በእሾኽ ስለምትሸፈን፤ ሰዎች ወደዚያ የሚገቡት ቀስትና ፍላጻ ይዘው ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገሪቱ በኲርንችትና በእሾኽ የተሞላች ስለ ሆነች ሕዝቡ ለአደን የሚወጣው ቀስትና ፍላጻ ይዞ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኵርንችትና እሾህ በምድር ሁሉ ላይ ነውና በፍላጻና በቀስት ወደዚያ ይገባሉ። |
በእሾህም ፋንታ ጥድ፥ በኵርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ የእግዚአብሔርም ስም ለዘለዓለም በማይጠፋ ምልክት ይመሰገናል።
በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል።
በሚታረሰውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍርሀት ይመጣል፤ የበጎች መሰማርያ ይሆናል፤ በሬዎችም ይረግጡታል፤ እሾህና ኵርንችትም ያጠፋዋል።
ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ይጠፋሉ፤ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”