ኢሳይያስ 7:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ ባመጣው ታላቅ ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን፣ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ፣ ማለትም በአሦር ንጉሥ፣ የራስና የእግር ጠጕራችሁን እንዲሁም ጢማችሁን ይላጫል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ፤ ማለትም በአሦር ንጉሥ፤ የራስና የእግር ጠጉራችሁን እንዲሁም ጢማችሁን ይላጫል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሠ ነገሥት የራሳችሁን የጢማችሁንና የሰውነታችሁን ሁሉ ጠጒር ይላጫል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፥ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል። |
“በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይነሣልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህም ዘንግ በሚመቱበት ላይ እንደ መነሣት፥ በትርም ዕንጨት አይደለሁም እንደ ማለት ነው።”
እግዚአብሔርም የግብፅን ባሕር ያደርቃል፤ በኀይለኛም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፤ ሰባት ፈሳሾችንም ይመታል፤ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል።
እንዲህም ሆነ፤ በንጉሡ በሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመተ መንግሥት የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ወሰዳቸው።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውኃ፥ የአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉ ያመጣባቸዋል፤ ወንዙም ሞልቶ ይወጣል፤ በዳሮቻቸውም ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤
አሁንስ የግዮንን ውኃ ትጠጪ ዘንድ በግብፅ መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ? የወንዞችንም ውኃ ትጠጪ ዘንድ በአሦር መንገድ ምን ጉዳይ አለሽ?
“የሰው ልጅ ሆይ! የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ሠራዊቱን በጢሮስ ላይ ጽኑ ሥራን አሠራቸው፤ ራስ ሁሉ የተላጨ፥ ጫንቃም ሁሉ የተላጠ ሆኖአል፤ ነገር ግን በላይዋ ስለ አሠራው ሥራ እርሱና ሠራዊቱ ከጢሮስ ደመወዝ አልተቀበሉም።
ስለ እኔ ሠርተዋልና በጢሮስ ላይ ስለ አገለገለው አገልግሎት የግብፅን ምድር ደመወዝ አድርጌ ሰጥቼዋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።