ስለዚህም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በዛንጅር ያዙት፤ በሰንሰለትም አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
ኢሳይያስ 7:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይመጡማል፤ እነርሱም ሁሉ በሸለቆ፥ በመንደሮች፥ በምድር ጕድጓድ፥ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በጫካ ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም በሙሉ መጥተው፣ በየበረሓው ሸለቆ፣ በየዐለቱ ንቃቃት፣ በየእሾኹ ቍጥቋጦና በየውሃው ጕድጓድ ሁሉ ይሰፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በሙሉ መጥተው፤ በየበረሓው ሸለቆ፤ በየዐለቱ ንቃቃት፤ በየእሾኩ ቁጥቋጦና በየውሃው ጉድጓድ ሁሉ ይሰፍራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እየተርመሰመሱ ወጥተው በበረሓው ሸለቆና በአለቱ ዋሻ ውስጥ በእሾኽ ቊጥቋጦና በከብት መሰማሪያ ግጦሽ ላይ ይሰፍራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይመጡማል፥ እነርሱም ሁሉ በበረሐ ሸለቆ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በእሾህ ቍጥቋጦ ሁሉ ላይ በማሰማርያውም ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ። |
ስለዚህም እግዚአብሔር የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አለቆች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በዛንጅር ያዙት፤ በሰንሰለትም አስረው ወደ ባቢሎን ወሰዱት።
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ያገቡአቸዋል።
እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ያገባሉ።
ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።
በእሾህም ፋንታ ጥድ፥ በኵርንችትም ፋንታ ባርሰነት ይበቅላል፤ የእግዚአብሔርም ስም ለዘለዓለም በማይጠፋ ምልክት ይመሰገናል።
በሚታረሰውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍርሀት ይመጣል፤ የበጎች መሰማርያ ይሆናል፤ በሬዎችም ይረግጡታል፤ እሾህና ኵርንችትም ያጠፋዋል።
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አድዳኞችን እልካለሁ፤ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድድኑአቸዋል።