እነርሱም አይጐዱትም፤ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ማንንም አይጐዱም፤ አያጠፉምም፤ ብዙ ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
ኢሳይያስ 66:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በምስጋና ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎዎች፥ በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰችው ከተማ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእግዚአብሔር ቍርባን እንዲሆኑ ወንድሞቻችሁን ሁሉ ከየመንግሥታቱ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም በፈረስ፣ በሠረገላና በጋሪ፣ በበቅሎና በግመል ያመጧቸዋል” ይላል እግዚአብሔር። “እስራኤላውያን የእህል ቍርባናቸውን በሥርዐቱ መሠረት በነጹ ዕቃዎች ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ እነዚህንም ያቀርቧቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ልጆች ቁርባናቸውን በጥሩ ዕቃ አድርገው ወደ ጌታ ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁም ለጌታ ቁርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎች በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቻችሁን ሁሉ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቅዱስ ተራራዬ በፈረሶች፥ በሠረገሎች፥ በጋሪዎች፥ በበቅሎዎችና በግመሎች አድርገው ከተለያዩ አገሮች ለእግዚአብሔር እንደ መባ ያመጡአቸዋል፤ እነርሱንም የሚያመጡአቸው እስራኤላውያን የእህል ቊርባንን በሥርዓት በነጻ ዕቃ ለእኔ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሚያቀርቡ አድርገው ነው፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በጥሩ ዕቃ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፥ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፥ በፈረሶችና በሰረገሎች፥ በአልጋዎችና በበቅሎች በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፥ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እነርሱም አይጐዱትም፤ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ማንንም አይጐዱም፤ አያጠፉምም፤ ብዙ ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
በኋላ ዘመን እንዲህ ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ቤት በተራሮች ራስ ላይ ይታያል፤ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛቡም ሁሉ ወደ እርሱ ይመጣሉ።
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
እንደ ገናምበቀኝና በግራ ተስፋፊ፤ ዘርሽ አሕዛብን ይወርሳሉና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ታደርጊያለሽና።
በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ ስም የሚያስጠራ ቦታን እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋ የዘለዓለም ስምንም እሰጣቸዋለሁ።”
ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና፥ የሚቃጠለው መሥዋዕታቸውና ቍርባናቸውም በመሠዊያዬ ላይ የተመረጠ ይሆናል።
“እናንተ ግን እኔን ተዋችሁኝ፤ ቅዱሱንም ተራራዬን ረሳችሁ፥ ለአጋንንትም ማዕድ አዘጋጃችሁ፤ ዕድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን ቀዳችሁ፤
ያንጊዜ ተኵላና በግ በአንድነት ይሰማራሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም፥” ይላል እግዚአብሔር።
መባቸውንም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ፤ የተከደኑ ስድስት ሰረገሎች ዐሥራ ሁለትም በሬዎች፤ በየሁለቱም አለቆች አንድ ሰረገላ አቀረቡ፤ ሁሉም እያንዳንዱ አንድ በሬ በድንኳኑ ፊት አቀረቡ።
በአሕዛብ መካከል ኢየሱስ ክርስቶስን አገለግል ዘንድ፥ ለእግዚአብሔር ወንጌልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትምህርት አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተወደደና የተመረጠ መሥዋዕት ይሆኑ ዘንድ።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።