La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 65:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከዚ​ያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚ​ኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድ​ሜ​ውን ያል​ፈ​ጸመ ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም፤ ጐል​ማ​ሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞ​ታ​ልና፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተ​ረ​ገመ ይሆ​ና​ልና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ከእንግዲህም በዚያ፣ ለጥቂት ጊዜ ብቻ በሕይወት የሚኖር ሕፃን፣ ወይም ዕድሜ ያልጠገበ አረጋዊ አይኖርም፤ አንድ መቶ ዓመት የሞላው ሰው ቢሞት፣ በዐጭር እንደ ተቀጨ ይቈጠራል፤ አንድ ሰው መቶ ዓመት ሳይሞላው ቢሞት፣ እንደ ተቀሠፈ ይገመታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጎልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ የመቶ ዓመት ሳይሆነው የሚሞት እንደተረገመ ኃጢአተኛ ይታያል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሕፃንነቱ የሚሞት ከቶ አይኖርም፤ ዕድሜውንም የማይፈጽም ሽማግሌ አይኖርም፤ በመቶ ዓመቱ የሚሞት ሰው በወጣትነቱ እንደ ሞተ ወጣት ከመቶ ዓመት በታች የሚሞት ሰው እንደ ተረገመ ይቈጠራል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፥ ጕልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና፥ ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 65:20
8 Referencias Cruzadas  

በወ​ራቱ የደ​ረሰ አዝ​መራ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ፥ የእ​ህሉ ነዶም በወ​ቅቱ ወደ አው​ድማ እን​ዲ​ገባ፥ በረ​ዥም ዕድሜ ወደ መቃ​ብር ትገ​ባ​ለህ።


ስለ በጎ ፋንታ ክፉን መለ​ሱ​ልኝ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ልጆ​ችን አሳ​ጡ​አት።


ይህም ነገር በሠ​ራ​ዊት ጌታ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጆሮ ተሰማ፥ “እስ​ክ​ት​ሞቱ ድረስ ይህ በደል በእ​ው​ነት አይ​ሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ሁም” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደ​ረ​ግ​በ​ታ​ልና ለበ​ደ​ለኛ ወዮ! ክፉም ይደ​ር​ስ​በ​ታል።


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዳግመኛ ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፣ ሰውም ሁሉ ከዕድሜው ብዛት የተነሣ ምርኩዝ በእጁ ይይዛል።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”