ኢሳይያስ 61:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘራቸው በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ያውቃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘሮቻቸው በመንግሥታት፣ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ፤ የሚያዩአቸውም ሁሉ፣ እግዚአብሔር የባረካቸው ሕዝብ እንደ ሆኑ ያውቃሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ ጌታ የባረከው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፥ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል። |
ላባም፥ “በዐይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚሁ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና።
በደረቅ መሬት ላይ ለሚሄድና ለተጠማ ውኃን እሰጣለሁ፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፥ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አኖራለሁ፤
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የያዕቆብ ቤት ሆይ! ደስ ይበላችሁ፤ በአሕዛብም አለቆች ላይ እልል በሉ፤ አውሩ፤ አመስግኑም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል በሉ።
የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት ሆይ፥ በአሕዛብ ዘንድ እርግማን እንደ ነበራችሁ፥ እንዲሁ አድናችኋለሁ፥ በረከትም ትሆናላችሁ፣ አትፍሩ፥ እጃችሁንም አበርቱ።
እግዚአብሔርም አስቀድሞ ልጁን አስነሣላችሁ፤ ሁላችሁም ከክፋታችሁ እንድትመለሱ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”