በክፉ ምክርሽ ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ ይነሡ፤ ያድኑሽም፤ ምን እንደሚመጣብሽም ይንገሩሽ፤
ኢሳይያስ 57:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፤ ዳግመኛም ጕልበት እያለኝ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን መንገድ አልተውም አላልሽም፤ ይህንም ስላደረግሽ አላፈርሽም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ ብዛት ደከምሽ፤ ነገር ግን ‘ተስፋ የለውም’ አላልሽም፤ የጕልበት መታደስ አገኘሽ፤ ስለዚህም አልዛልሽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፤ የጉልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ መንከራተታችሁ የተነሣ ትደክማላችሁ፤ ሆኖም ግን ፍላጎታችሁ በጣም ስለ ተነሣሣ “ጠቃሚ አይደለም” ብላችሁ አላቆማችሁም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፥ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም። |
በክፉ ምክርሽ ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ ይነሡ፤ ያድኑሽም፤ ምን እንደሚመጣብሽም ይንገሩሽ፤
እነርሱ ግን፥ “እንጨክናለን፤ ክዳታችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም ክፉ ልባችንን ደስ የሚያሰኛትን እናደርጋለን” አሉ።
እግርሽን ከሰንከልካላ መንገድ፥ ጕሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ እርስዋ ግን፥ “እጨክናለሁ፤ እንግዶችንም ወድጄአለሁ” ብላ ተከተለቻቸው።
ለጕስቍልናሽ ከብዙዎች እረኞች ጋር ኖርሽ የአመንዝራም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ በሁሉም ዘንድ ያለ ኀፍረት ሄድሽ። ስለዚህ የመከርና የበልግ ዝናም ተከለከለ።
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
እያንዳንዱ በባልንጀራው ላይ ይሣለቃል በእውነትም አይናገርም፤ ሐሰት መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፤ በደሉ መመለስንም እንቢ አሉ።