ኢሳይያስ 53:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉዎችንም ስለ መቃብሩ፥ ባለጸጎችንም ስለ ሞቱ እሰጣለሁ፤ ኀጢአትን አላደረገምና፥ ከአፉም ሐሰት አልተገኘበትምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአፉም ሳያታልል፣ ዐመፃም ሳያደርግ፣ አሟሟቱ ከክፉዎች፣ መቃብሩም ከባለጠጎች ጋራ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሟሟቱን ከክፉዎችም ጋር፥ መቃብሩን ከባለጠጎችም ጋር አደረጉ፤ ግፍ ግን አላደረገም ነበር፤ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ዐመፅ ሳይፈጽም፥ በአንደበቱም ሐሰት ሳይገኝበት፥ በሞቱ ከክፉ አድራጊዎች ጋር ተቈጠረ፤ በባለጸጋም መቃብር ተቀበረ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፥ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር። |
ሊቀ ካህናታችን ለድካማችን መከራ መቀበልን የማይችል አይደለምና፤ ነገር ግን ከብቻዋ ከኀጢአት በቀር እኛን በመሰለበት ሁሉ የተፈተነ ነው።
ቅዱስና ያለ ተንኰል፥ ነውርም የሌለበት፥ ከኀጢአተኞችም የተለየ፥ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል።