ኢሳይያስ 50:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይጎዳኛል? እነሆ፥ ሁላችሁ እንደ ልብስ ታረጃላችሁ፤ ብልም ይበላችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚረዳኝ እርሱ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የሚፈርድብኝስ ማን ነው? እነሆ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ ብልም ይበላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፤ ማን ይፈርድብኛል? እነሆ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚረዳኝ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ ማን ይፈርድብኛል? ከሳሾቼ እንደ ልብስ ያረጃሉ፤ ብልም ይበላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል፥ ማን ይፈርድብኛል? እነሆ፥ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል። |
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ እንዲከናወን አላደርግም፤ በአንቺ ላይ ለፍርድ የሚነሣውን ድምፅ ሁሉ ታጠፊያለሽ፤ ጠላቶችሽም ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ እግዚአብሔርንም ለሚያገለግሉ ርስት አላቸው፤ ጻድቃኔም ትሆኑኛላችሁ ይላል እግዚአብሔር።