ኢሳይያስ 46:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ በማን ትመስሉኛላችሁ? የምትሳሳቱ እናንተ ሁላችሁ፥ እዩ፤ አስተውሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከማን ጋራ ታወዳድሩኛላችሁ? ከማንስ ጋራ እኩል ታደርጉኛላችሁ? እንመሳሰልስ ዘንድ ከማን ጋራ ታነጻጽሩኛላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከማን ጋር ታወዳድሩኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር አመሳስላችሁ ታወዳድሩኛላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ? |
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
የያዕቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፤ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ነውና እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።