ኢሳይያስ 45:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበሩትን መዛግብት እሰጥሃለሁ፤ የማይታየውንም የተደበቀውን ሀብት እገልጥልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ፣ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቅ ዘንድ፣ በተሰወረ ስፍራ የተከማቸውን ሀብት፣ በጨለማም ያለውን ንብረት እሰጥሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እኔ እንደሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨለማና በድብቅ ቦታ የተከማቸውን ሀብት እሰጥሃለሁ። በዚህም በስምህ የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንኩ ታውቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ። |
“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤትን እሠራለት ዘንድ እንዳስብ አደረገኝ፤
ሙሴም እግዚአብሔርን፥ “እነሆ፥ አንተ፦ ይህን ሕዝብ አውጣ ትለኛለህ፤ ነገር ግን ከእኔ ጋር የምትልከውን አላስታወቅኸኝም። አንተም ከሁሉ ይልቅ ዐወቅሁህ፥ ደግሞም በእኔ ፊት ሞገስን አገኘህ አልኸኝ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ይህን ያልኸኝን ነገር አደርግልሃለሁ፤ በፊቴ ሞገስን አግኝተሀልና ከሁሉ ይልቅ ዐውቄሃለሁና”አለው።
አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እናደንቃችሁም ዘንድ፥ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዝአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ተቤዥችሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።
ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተም አሕዛብ፥ አድምጡ፤ ከረዥም ዘመን በኋላ እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፤ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠርቶአል፤
በዚያም የተገኙ ዐሥር ሰዎች ቀርበው እስማኤልን እንዲህ አሉት፥ “በሜዳው ድልብ አለንና፥ ገብስና ስንዴ፥ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን፤” እርሱም በወንድሞቻቸው መካከል እነርሱን መግደል ተወ።
ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ፥ በመካከልዋም በተቀላቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በመዝገቦችዋ ላይ አለ፤ ይበተናሉም።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።