La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 44:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብረት ሠሪ መጥ​ረ​ቢ​ያ​ውን ይስ​ላል፤ ጣዖ​ቱን በመ​ጥ​ረ​ቢያ ይቀ​ር​ጸ​ዋል፤ በመ​ዶ​ሻም መትቶ ቅርጽ ይሰ​ጠ​ዋል፤ በክ​ን​ዱም ኀይል ይሠ​ራ​ዋል፤ እር​ሱም ይራ​ባል፤ ይደ​ክ​ም​ማል፤ ውኃም አይ​ጠ​ጣም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የብረት የእጅ ጥበብ ባለሙያ መሥሪያን ይይዛል፤ በከሰል ፍም ላይ ይሠራዋል፤ ጣዖትን በመዶሻ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ በክንዱም ኀይል ያበጀዋል። ከዚያም ይራባል፤ ጕልበት ያጣል፤ ውሃ ይጠማል፤ ይደክማል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፥ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፥ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሠጠዋል፤ በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፥ እርሱም ይርበዋል ይደክማልም፤ ውኃም ለመጠጣት ይታክታል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንጥረኛ ጣዖትን ለመሥራት ብረትን ወስዶ በእሳት ያቀልጠዋል። ለብረቱም ቅርጽ ለመስጠት በብርቱ ክንዱ በመዶሻ ይቀጠቅጠዋል፤ ይህንንም በሚሠራበት ጊዜ ይራባል፥ ይጠማል፥ ይደክማልም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፥ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፥ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሠጠዋል፥ በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፥ እርሱም ይራባል ይደክምማል፥ ውኃም አይጠጣም ይታክትማል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 44:12
11 Referencias Cruzadas  

ከእ​ጃ​ቸ​ውም ተቀ​ብሎ በመ​ቅ​ረጫ ቀረ​ጸው፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ጥጃም አደ​ረ​ገው፤ እር​ሱም፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እነ​ዚህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጡህ አማ​ል​ክ​ትህ ናቸው” አላ​ቸው።


ካዘ​ዝ​ኋ​ቸው መን​ገድ ፈጥ​ነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተ​ሠራ የጥጃ ምስል ለራ​ሳ​ቸው አደ​ረጉ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም፤ ሠዉ​ለ​ትም፤


እን​ጨት ጠራቢ በሠ​ራው ምስል፥ ወይስ አን​ጥ​ረኛ መትቶ በሠ​ራው ወርቅ፥ በወ​ር​ቅም ለብጦ በሠ​ራው ምስል ትመ​ስ​ሉ​ታ​ላ​ች​ሁን?


ጠራ​ቢው የማ​ይ​ነ​ቅ​ዘ​ውን እን​ጨት ይመ​ር​ጣል፤ ምስ​ሉም እን​ዳ​ይ​ና​ወጥ ያቆ​መው ዘንድ ብልህ ሠራ​ተ​ኛን ይፈ​ል​ጋል።


እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?


የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?


እግዚአብሔርም አራት ጠራቢዎች አሳየኝ።


በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ።