ይምጡ፤ የሚደርስባችሁንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ፤ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ንገሩን፤ የሚመጡትንም አሳዩን።
ኢሳይያስ 41:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናውቅ ዘንድ፥ ከጥንት የተነገረው፦ እውነት ነው እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? ከመሆኑ በፊት የሚናገር የለም፤ የሚገልጥም የለም፤ ቃላችሁን የሚሰማ የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛ እናውቅ ዘንድ ይህን ከመጀመሪያው የተናገረ፣ ‘እርሱ ትክክል ነው’ እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረ ማነው? ማንም አልተናገረም፤ ቀደም ብሎ የተናገረ የለም፤ ቃላችሁንም የሰማ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እድናውቀው ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው፥ እንድንልም ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናውቀው ዘንድና ትክክል ነው እንል ዘንድ ከመጀመሪያ ጀምሮ ይህን የተናገረ ማነው? ስለዚህ ጉዳይ መግለጫ የሰጠ፥ ወይም ያወጀ፥ ከእናንተም አንድ ቃል የተናገረ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው፦ እውነት ነው እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፥ የሚገልጥም የለም፥ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም። |
ይምጡ፤ የሚደርስባችሁንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ፤ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ንገሩን፤ የሚመጡትንም አሳዩን።
አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አለቆችም ተከማቹ፤ ይህን ማን ይናገራል? የቀድሞውንስ ማን ይነግራችኋል? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፤ ሰምተውም፦ እውነትን ይናገሩ።
እንደ እኔ ያለ አዳኝ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ፤ ይናገርም፤ ሰውን ከፈጠርሁበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለሙ የሚሆነውን ያዘጋጅልኝ፤ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይናገር።
የሚናገሩ ከሆነ ከጥንት ጀምሮ ይህን ምስክርነት ያደረገ ማን እንደ ሆነ በአንድነት ያውቁ ዘንድ ይቅረቡ። ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኀኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።
እኔ አምላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለምና የቀድሞውንና የጥንቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።