Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 41:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ይምጡ፤ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁ​ንም ይን​ገ​ሩን፤ ልብም እና​ደ​ርግ ዘንድ፤ ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ው​ንም እና​ውቅ ዘንድ፥ የቀ​ደ​ሙት ነገ​ሮች ምን እንደ ሆኑ ንገ​ሩን፤ የሚ​መ​ጡ​ት​ንም አሳ​ዩን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 “የሚሆነውን እንዲነግሩን፣ ጣዖቶቻችሁን አምጡ፤ እንድንገነዘብ፣ ፍጻሜአቸውን እንድናውቅ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ነበሩ ንገሩን፤ ስለሚመጡትም ነገሮች ግለጹልን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እድናደርግ፥ ፍጻሜአቸውንም እድናውቅ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ጣዖቶቻችሁንም አምጡና በሚፈጸምበት ጊዜ እንድናውቀው ወደ ፊት የሚሆነውን ሁሉ እስቲ ይንገሩን፤ ወደፊት ውጤታቸው ምን እንደሚሆን አስተውለን እንረዳ ዘንድ የቀድሞዎቹ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ይንገሩን፤ ወይም ወደፊት ምን እንደሚከሠት ያስረዱን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ያምጡ፥ የሚሆነውንም ይንገሩን፥ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደሆኑ ተናጋሩ፥ የሚመጡትንም አሳዩን።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 41:22
11 Referencias Cruzadas  

የሚ​ና​ገሩ ከሆነ ከጥ​ንት ጀምሮ ይህን ምስ​ክ​ር​ነት ያደ​ረገ ማን እንደ ሆነ በአ​ን​ድ​ነት ያውቁ ዘንድ ይቅ​ረቡ። ያሳ​የ​ሁም የተ​ና​ገ​ር​ሁም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አም​ላ​ክና መድ​ኀ​ኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ይሰ​ማሉ፤ ይህን ማን ነገ​ራ​ቸው? አን​ተን በመ​ው​ደድ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ዘር አስ​ወ​ግድ ዘንድ ፈቃ​ድ​ህን በባ​ቢ​ሎን ላይ አደ​ረ​ግሁ።


በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ።


እንደ እኔ ያለ አዳኝ ማን ነው? ይነ​ሣና ይጥራ፤ ይና​ገ​ርም፤ ሰውን ከፈ​ጠ​ር​ሁ​በት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያዘ​ጋ​ጅ​ልኝ፤ የሚ​መ​ጣ​ውም ነገር ሳይ​ደ​ርስ ይና​ገር።


እር​ሱም እኔን ያከ​ብ​ረ​ኛል፤ ከእኔ ወስዶ ይነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ልና።


በሆ​ነም ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከዛሬ ጀምሮ ከመ​ሆኑ አስ​ቀ​ድሞ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


እነሆ የቀ​ድ​ሞው ነገር ተፈ​ጸመ፤ አዲስ ነገ​ር​ንም እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም ሳይ​ነ​ገር እር​ሱን አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ።”


እና​ውቅ ዘንድ፥ ከጥ​ንት የተ​ነ​ገ​ረው፦ እው​ነት ነው እን​ልም ዘንድ ቀድሞ የተ​ና​ገ​ረው ማን ነው? ከመ​ሆኑ በፊት የሚ​ና​ገር የለም፤ የሚ​ገ​ል​ጥም የለም፤ ቃላ​ች​ሁን የሚ​ሰማ የለም።


የቀ​ድ​ሞ​ውን ነገር ከጥ​ንት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ከአ​ፌም ወጥ​ቶ​አል፤ ድን​ገ​ትም ያደ​ረ​ግ​ሁት ምስ​ክር ሆኖ​አል፤ እር​ሱም ተፈ​ጽ​ሞ​አል።


እና​ንተ በም​ድር ዳርቻ ያላ​ችሁ ሁሉ፥ እኔ አም​ላክ ነኝና፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለ​ምና ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ ትድ​ኑ​ማ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios