ኢሳይያስ 41:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደሴቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመለሱ፤ አለቆች ኀይላቸውን ያድሳሉና በአንድነት ቀርበው ፍርድን ይናገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደሴቶች ሆይ፤ በፊቴ ዝም በሉ፤ አሕዛብ ኀይላቸውን ያድሱ! ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድም ፊት እንገናኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፤ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በደሴቶች የምትኖሩ ሕዝቦች! ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! ሕዝቦች ኀይላቸውን ያድሱ፤ ወደ ፊትም ቀርበው ይናገሩ፤ በፍርድ ሸንጎ በአንድነት እንገናኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደሴቶች ሆይ፥ በፊቴ ዝም በሉ፥ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፥ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፥ ለፍርድ በአንድነት እንቅረብ። |
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከባቢሎንና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላሜጤን፥ ከምሥራቅና ከምዕራብ ለቀሩት ለሕዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
እናንተ አሕዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እናንተም አለቆች ሆይ፥ አድምጡ፤ ምድርና በውስጥዋም ያሉ፥ ዓለምና በውስጥዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።
እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉና የሚታገሡ ግን ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር ክንፍ ያወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱምም፤ ይሄዳሉ፤ አይራቡምም።
አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አለቆችም ተከማቹ፤ ይህን ማን ይናገራል? የቀድሞውንስ ማን ይነግራችኋል? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፤ ሰምተውም፦ እውነትን ይናገሩ።
ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፤ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተም አሕዛብ፥ አድምጡ፤ ከረዥም ዘመን በኋላ እንዲህ ይሆናል ይላል እግዚአብሔር፤ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን ጠርቶአል፤
የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው፤ ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? እስቲ በእኔ ላይ ይነሣ፤ የሚከራከረኝስ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።