La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 38:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ በአ​ባ​ትህ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀ​ሐይ ጋራ የወ​ረ​ደ​ውን በደ​ረ​ጃ​ዎች ያለ​ውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እን​ዲ​መ​ለስ አደ​ር​ጋ​ለሁ።” ፀሐ​ይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወ​ረ​ደ​በት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመ​ለሰ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአካዝ የሰዓት መቍጠሪያ ደረጃ ላይ፣ የወረደውን የፀሓይ ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።’ ” ስለዚህ ወርዶ የነበረው የፀሓይ ጥላ ያንኑ ያህል ወደ ኋላ ተመለሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍራ ሰዓት መቁጠሪያ ላይ በደረጃዎች ያለውን ከፀሐይ ጋር የወረደውን ጥላ በዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላው የሰዓት ስፍራ ላይ በወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንጉሥ አካዝ ባሠራው የመወጣጫ ደረጃ ላይ የሚያርፈውን ጥላ እግዚአብሔር እንደገና ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ እንዲመለስ ያደርገዋል።” ጥላውም ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ ተመለሰ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ በአካዝ የጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ አሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ። ፀሐይም በጥላ ስፍረ ሰዓት ላይ የወረደበት አሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 38:8
8 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ እስከ ሞት ድረስ ታመመ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ፤ እር​ሱም ሰማው፤ ምል​ክ​ትም ሰጠው።


ነገር ግን የባ​ቢ​ሎን መሳ​ፍ​ንት መል​እ​ክ​ተ​ኞች በሀ​ገሩ ላይ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ም​ራት ይጠ​ይ​ቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተ​ላኩ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ነ​ውና በልቡ ያለ​ውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።


የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ ከደ​ዌው በተ​ፈ​ወሰ ጊዜ የጸ​ለ​የው ጸሎት ይህ ነው፦


“ከጥ​ልቁ ወይም ከከ​ፍ​ታው ቢሆን ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምል​ክ​ትን ለአ​ንተ ለምን።”


ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ “በፊ​ትህ ሞገ​ስን ካገ​ኘሁ፥ የም​ት​ና​ገ​ረ​ኝም አንተ እንደ ሆንህ ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ፤