La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 36:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብትል፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በዚህ መሥ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም፣ “በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን” የምትለኝ ከሆነ፣ የኰረብታ ላይ ማምለኪያዎቹንና መሠዊያዎቹን ሕዝቅያስ አፍርሶበት ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም፣ “እናንተ መስገድ ያለባችሁ በዚህ መሠዊያ ፊት ብቻ ነው” ብሎ የለምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተም፦ ‘በአምላካችን በጌታ እንታመናለን’ ብትለኝ፥ ‘በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ’ ብሎ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ሕዝቅያስ ያስፈረሰው እርሱ አይደለምን?

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአሦራውያን ባለ ሥልጣን ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ ‘እኔ የምታመነው በአምላኬ በእግዚአብሔር ነው’ ትል ይሆናል፤ ታዲያ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በዚህ በአንድ መሠዊያ ብቻ እንዲያመልኩ ፈልገህ የእግዚአብሔርን መሠዊያዎችና የማምለኪያ ስፍራዎች ያፈራረስክ አንተ ሕዝቅያስ አይደለህምን?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተም፦ በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን ብትለኝ፥ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን፦ በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ያስፈረሰ ይህ አይደለምን?

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 36:7
15 Referencias Cruzadas  

እና​ን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብት​ሉኝ፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?


በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።


ተነ​ሥ​ተ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችና ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ያ​ጥ​ኑ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ አስ​ወ​ገዱ፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ ጣሉት።


ይህም ሁሉ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ገኙ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወጥ​ተው ዐም​ዶ​ቹን ሰበሩ፤ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ች​ንም አፈ​ረሱ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አጠፉ። በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ሁሉ ደግ​ሞም በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ የነ​በ​ሩ​ትን ፈጽ​መው እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ አጠ​ፉ​አ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስ​ታ​ቸ​ውና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ተመ​ለሱ።


በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ዕጠኑ፤ እያለ የይ​ሁ​ዳን ሕዝ​ብና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች አዝዞ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያፈ​ረሰ ይህ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?


ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝ​ኛ​ለሽ? ለም​ንስ ታው​ኪ​ኛ​ለሽ? የፊ​ቴን መድ​ኀ​ኒት አም​ላ​ኬን አመ​ሰ​ግ​ነው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመኚ።


አሁን እን​ግ​ዲህ ከጌ​ታዬ ከአ​ሦር ንጉሥ ጋር ተስ​ማማ፤ የሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ው​ንም ሰዎች ማግ​ኘት ቢቻ​ልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረ​ሶ​ችን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ።


መን​ፈስ ቅዱስ ያደ​ረ​በት ሰው ግን ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፤ እር​ሱን ግን የሚ​መ​ረ​ም​ረው የለም።