Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 32:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ዕጠኑ፤ እያለ የይ​ሁ​ዳን ሕዝ​ብና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች አዝዞ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ችና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያፈ​ረሰ ይህ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም፣ ‘በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፤ በላዩም መሥዋዕት አቃጥሉ’ በማለት የራሱን አምላክ የኰረብታ ላይ መስገጃ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችንስ ያስወገደ ሕዝቅያስ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 “በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፥ በእርሱም ላይ ዕጠኑ” እያለ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አዝዞ፥ የኮረብታው መስገጃዎቹና መሠዊያዎቹን ያፈረሰ ይህ ሕዝቅያስ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ ቀደም የተቀደሱትን የእግዚአብሔርን ማምለኪያ ስፍራዎችና መሠዊያዎችን ያፈራረሰ፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብም በአንድ መሠዊያ ላይ ብቻ ዕጣን እያጠነ እንዲሰግድ ያደረገ ሕዝቅያስ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 “በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፤ በእርሱም ላይ ዕጠኑ” እያለ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አዝዞ፥ የኮረብታው መስገጃዎቹና መሠዊያዎቹን ያፈረሰ ይህ ሕዝቅያስ አይደለምን?

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 32:12
14 Referencias Cruzadas  

ይህም ሁሉ በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ በይ​ሁዳ ከተ​ሞች የተ​ገኙ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወጥ​ተው ዐም​ዶ​ቹን ሰበሩ፤ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ኮረ​ብ​ታ​ዎ​ች​ንም አፈ​ረሱ፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም አጠፉ። በይ​ሁ​ዳና በብ​ን​ያ​ምም ሁሉ ደግ​ሞም በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ የነ​በ​ሩ​ትን ፈጽ​መው እስከ ዘለ​ዓ​ለሙ አጠ​ፉ​አ​ቸው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ርስ​ታ​ቸ​ውና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ተመ​ለሱ።


አን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብትል፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በዚህ መሥ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?


ርዝ​መ​ቱም ሃያ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ክንድ፥ ቁመ​ቱም ዐሥር ክንድ የነ​በ​ረ​ውን የና​ሱን መሠ​ዊያ ሠራ።


እና​ን​ተም፦ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ታ​መ​ና​ለን ብት​ሉኝ፥ ሕዝ​ቅ​ያስ ይሁ​ዳ​ንና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን፦ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በዚህ መሠ​ዊያ ፊት ስገዱ ብሎ የኮ​ረ​ብታ መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቹ​ንና መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹን ያስ​ፈ​ረሰ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን?


በኮ​ረ​ብ​ታም ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎች አስ​ወ​ገደ፤ ሐው​ል​ቶ​ች​ንም ሰባ​በረ፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ች​ንም ነቃ​ቀለ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስ​ከ​ዚህ ዘመን ድረስ ያጥ​ኑ​ለት ነበ​ርና ሙሴ የሠ​ራ​ውን የና​ሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙ​ንም “ነሑ​ስ​ታን” ብሎ ጠራው።


ሰሎ​ሞ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ዕቃን ሁሉ አሠራ፤ የወ​ር​ቁን መሠ​ዊያ፥ የገ​ጹም ኅብ​ስት የነ​በ​ረ​በ​ትን የወ​ርቅ ገበታ፥


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ያድ​ነ​ናል እያለ ለራብ፥ ለጥ​ምና ለሞት አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሚ​ያ​ሳ​ስ​ታ​ችሁ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?


ለክ​ብ​ርህ ከፍ​ተ​ኛ​ነት ፍጻሜ የለ​ው​ምና፥ የቍ​ጣ​ህም መቅ​ሠ​ፍት በኃ​ጥ​አን ላይ ግሩም ነው።


ተነ​ሥ​ተ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችና ለጣ​ዖ​ታት የሚ​ያ​ጥ​ኑ​በ​ትን ዕቃ ሁሉ አስ​ወ​ገዱ፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ወንዝ ጣሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios