እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደንቆሮስ፥ የሚያይስ፥ ዕውርስ የሚያደርግ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ኢሳይያስ 32:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደካሞች ሰዎች ልብ ዕውቀትን ትሰማለች፤ የተብታቦችም ምላስ ፈጥና የሰላምን ነገር ትማራለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የችኵል አእምሮ ያውቃል፤ ያስተውላልም፤ የተብታባም ምላስ የተፈታ ይሆናል፤ አጥርቶም ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፤ የተብታቦችም ምላስ ተፍታታና ደኅና አድርጋ ትናገራለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ችኲሎች የነበሩ በትዕግሥት የሚያመዛዝኑ ይሆናሉ፤ ተብታባ አንደበት የነበራቸው አንደበተ ርቱዖች ይሆናሉ፤ ንግግራቸውም ግልጥ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፥ የተብታቦችም ምላስ ደኅና አድርጋ ትናገራለች። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “ለሰው አፍን የሰጠ ማን ነው? ዲዳስ፥ ደንቆሮስ፥ የሚያይስ፥ ዕውርስ የሚያደርግ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን?
ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፉንም እይዛለሁ አልሁ፤ ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ ናቸው፥ የአፍንጫሽም ሽታ እንደ እንኮይ ነው።
በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፤ የሚያጕረመርሙም መታዘዝን ይማራሉ፤ ዲዳ አንደበትም ሰላም መናገርን ይማራል።”
እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ጴጥሮስና ዮሐንስም ግልጥ አድርገው ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፥ ያልተማሩና መጽሐፍን የማያውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐውቀው አደነቁ፤ ሁልጊዜም ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።
የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢየሩሳሌምም ምእመናን እጅግ በዙ፤ ከካህናትም መካከል ያመኑ ብዙዎች ነበሩ።
ነገር ግን “ቀድሞ ምእመናንን ያሳድድ የነበረው እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን የሃይማኖት ትምህርት ዛሬ ይሰብካል” ሲባል ወሬዬን ይሰሙ ነበር።