እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
ኢሳይያስ 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያሉንም፥ ተዋጊውንም፥ ፈራጁንም፥ ነቢዩንም፥ ዐዋቂውንም፥ ሽማግሌውንም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጀግናውንና ተዋጊውን፣ ፈራጁንና ነቢዩን፣ አስማተኛውንና ሽማግሌውን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጀግናውንና ተዋጊውን፤ ፈራጁንና ነቢዩን፤ አስማተኛውንና ሽማግሌውን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጀግኖቻቸውን፥ ወታደሮቻቸውን፥ ዳኞቻቸውንና ነቢያታቸውን፥ ሟርተኞቻቸውንና ሽማግሌዎቻቸውን፥ የጦር መኰንኖቻቸውንና አማካሪዎቻቸውን፥ ጠንቋዮቻቸውንና የወደፊቱን እናውቃለን የሚሉትን ሁሉ ነቃቅሎ ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያሉንም፥ ተዋጊውንም፥ ፈራጁንም፥ ነብዩንም፥ ምዋርተኛውንም፥ ሽማግሌውንም፥ |
እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
የአምሳ አለቃውንም፥ የተከበረ አማካሪውንም፥ ጠቢቡንም፥ የአናጢዎቹንም አለቃ፥ አስተዋይ አድማጩንም ያስወግዳል።
“የሰው ልጅ ሆይ፥ ለአስቈጡኝ ለእስራኤል ቤት ይህ ትርጓሜ ምን እንደ ሆነ አታውቁምን? በላቸው። እንዲህም ብለህ ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፤ ንጉሥዋንና መኳንንቶችዋንም ማረከ፤ ወደ ሀገሩም ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች በስውር እያንዳንዱ በሥዕሉ ቤት የሚያደርጉትን አይተሃልን? እነርሱ እግዚአብሔር አያየንም፤ እግዚአብሔር ምድሪቱን ትቶአታል ይላሉና” አለኝ።