ኢሳይያስ 23:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደሴት የሚኖሩ በባሕር የሚሻገሩ የፊኒቄ ስደተኞች ምን ይመስላሉ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የባሕር ተጓዦች ያበለጠጓችሁ፣ በደሴቲቱ የምትኖሩ፣ የሲዶና ነጋዴዎችም ጸጥ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፥ በባሕርም የሚሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች የሞሉባችሁ፥ ጸጥ በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መርከበኞች ያበለጸጉአችሁ እናንተ የደሴቲቱ ሕዝብና የሲዶን ነጋዴዎች በሐዘን ጸጥ በሉ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በደሴት የምትኖሩ በባህርም የሚሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች ንግድ የሞሉባችሁ ሆይ፥ ጸጥ በሉ። |
የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፥ “የመንግሥታት እመቤት” አትባዪምና በድንጋጤ ዝም ብለሽ ተቀመጪ፤ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! የጢሮስን አለቃ እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልብህ ኰርትዋል፥ አንተ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እግዚአብሔርም በባሕር መካከል እንዲቀመጥ እኔም ተቀምጫለሁ ብለሃልና፤ አንተ ሰው ስትሆን ልብህን እንደ እግዚአብሔር ልብ ብታደርግም አንተ እግዚአብሔር አይደለህም።