ኢሳይያስ 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤ ምሽጋችሁ ፈርሷል! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በባሕር ላይ የምትመላለሱ የተርሴስ መርከበኞች! የምትኰሩባት ወደብ ስለ ተደመሰሰች በዋይታ አልቅሱ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ። |
ስለ ጢሮስ የተነገረ ትንቢት። የኬልቀዶን መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ጠፍተዋልና፤ እንግዲህም ከኬጤዎን ሀገር አይመጡምና ማርከውም ይወስዱአቸዋልና።