እንጀራ ይዛችሁ ከሰልፍ ከሸሹ ከብዙ ሰዎችና በጦር ከጠፉ ከብዙ ሰዎች፥ ፍላጻ ከያዙ ከብዙ ሰዎችና ጦር ከያዙ ከብዙ ሰዎች፥ ቀስቶቻቸው ከተሳቡና በሰልፍ ከወደቁ ከብዙ ሰዎች ያመለጡትን ተቀበሏቸው።
ኢሳይያስ 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አለቆችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፤ የተማረኩትንም በእግር ብረት አሠቃዩአቸው፤ ኀይለኞችሽም ርቀው ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሪዎችሽ በሙሉ በአንድ ላይ ሸሽተዋል፤ ቀስት እንኳ ሳያነሡ ተማርከዋል፤ ጠላት ገና በሩቅ ሳለ የሸሻችሁ ሁሉ፣ ተይዛችሁ በአንድነት ታስራችኋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፥ ያለ ቀስትም ተማረኩ፤ እርቀው ቢሸሹም አንቺ ጋር የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መሪዎችሽ በሙሉ አንዲት ፍላጻ ሳይወረውሩ በሽሽት ላይ እንዳሉ ተማረኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አለቆችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፥ ያለ ቀስትም ተማረኩ፥ ከሩቅ ሸሽተው ከአንቺ ዘንድ የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ። |
እንጀራ ይዛችሁ ከሰልፍ ከሸሹ ከብዙ ሰዎችና በጦር ከጠፉ ከብዙ ሰዎች፥ ፍላጻ ከያዙ ከብዙ ሰዎችና ጦር ከያዙ ከብዙ ሰዎች፥ ቀስቶቻቸው ከተሳቡና በሰልፍ ከወደቁ ከብዙ ሰዎች ያመለጡትን ተቀበሏቸው።
በዚያም ቀን ይላል እግዚአብሔር፤ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይጠፋል፤ ካህናቱም ይደነግጣሉ፤ ነቢያቱም ያደንቃሉ።