የተረፉትም ሁሉ እንደ ተባረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆናሉ። የሚሰበስባቸውም የለም፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸሻል።
ኢሳይያስ 21:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንጀራ ይዛችሁ ከሰልፍ ከሸሹ ከብዙ ሰዎችና በጦር ከጠፉ ከብዙ ሰዎች፥ ፍላጻ ከያዙ ከብዙ ሰዎችና ጦር ከያዙ ከብዙ ሰዎች፥ ቀስቶቻቸው ከተሳቡና በሰልፍ ከወደቁ ከብዙ ሰዎች ያመለጡትን ተቀበሏቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰይፍ፣ ከተመዘዘ ሰይፍ፣ ከተደገነ ቀስት፣ ከተፋፋመ ጦርነት ሸሽተዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰይፍ፥ ከተመዘዘው ሰይፍ፥ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ሁሉ ከሚገደሉበት ሰይፍ፥ ከተደገነባቸው ቀስትና ከጦርነት አደጋ ሁሉ ለማምለጥ በመሸሽ ላይ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰይፍ፥ ከተመዘዘው ሰይፍ፥ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና። |
የተረፉትም ሁሉ እንደ ተባረረ ሚዳቋ፥ እንደ ባዘነ በግም ይሆናሉ። የሚሰበስባቸውም የለም፤ እንዲሁም ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ ሁሉም ሰው ወደ ሀገሩ ይሸሻል።
ብዙዎች አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ናቸው፤ ከፏፏቴ ውስጥ በኀይል እንደሚወርድ እንደ ብዙ ውኃ ፈሳሽ ይጮኻሉ፤ ያጠፉታልም፤ እነርሱም ከሩቅ ይወርዳሉ፤ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፥ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው እንደ መንኰራኵር ትቢያም ይበተናሉ።
ነገር ግን አለቆችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፤ የተማረኩትንም በእግር ብረት አሠቃዩአቸው፤ ኀይለኞችሽም ርቀው ሸሹ።
አሦርም ይወድቃል፤ የሚወድቀውም በሰው ሰይፍ አይደለም፤ የምትበላቸውም የሰው ሰይፍ አይደለችም፤ የሚሸሹም ከሰይፍ ፊት አይደለም ጐልማሶቻቸው ግን ይሸነፋሉ።