አዳኝህ እግዚአብሔርን ትተኸዋልና፥ ረዳትህ እግዚአብሔርንም አላስብኸውም፤ ስለዚህ የሐሰትን ተክል ተክለሃል፤ የሐሣርንም ዘር ዘርተሃል።
ኢሳይያስ 17:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን በእስራኤል ልጆች ፊት የአሞራውያንና የኤዌዎያውያን ከተሞች እንደ ተፈቱ፥ እንዲሁ ከተሞችህ ይፈታሉ፤ ባድማም ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን በእስራኤል ልጆች ምክንያት የተተዉት ጠንካራ ከተሞች ጥሻና ውድማ እንደ ሆኑ ሁሉ፣ እነዚህ ሁሉ ባድማ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን በእስራኤል ልጆች ምክንያት የአሞራውያንና የኤዊያውያን ከተሞች ምድረ በዳ እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ጠንካራ ከተሞችህ ባድማም ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እስራኤላውያን አደጋ ባደረሱባቸው ጊዜ የሒዋውያንና የአሞራውያን ከተሞች ባድማ እንደ ሆኑት የእናንተም ጠንካራ ከተሞች ባድማዎች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን በእስራኤል ልጆች ፊት የአሞራውያንና የኤዊያውያን ከተሞች እንደ ተፈቱ፥ እንዲሁ ከተሞችህ ይፈታሉ፥ ባድማም ይሆናሉ። |
አዳኝህ እግዚአብሔርን ትተኸዋልና፥ ረዳትህ እግዚአብሔርንም አላስብኸውም፤ ስለዚህ የሐሰትን ተክል ተክለሃል፤ የሐሣርንም ዘር ዘርተሃል።
በጣዖታቸውና ጣቶቻቸው በሠሩአቸው የእጃቸው ሥራዎች አይተማመኑም፤ ለርኵሰታቸውም ዛፎችን አይቈርጡም።
በዚያም የተሰማራው መንጋ እንደ ተተወ መንጋ ይሆናል፤ ምድሩም ለብዙ ዘመን መሰማሪያ ይሆናል፤ በዚያም መንጋው ይሰማራል፤ ያርፋልም።
በሕዝብህም መካከል ጥፋት ይነሣል፤ እናትም በልጆችዋ ላይ በተጣለች ጊዜ የሰልማን አለቃ ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።
መሳቂያ የሆኑ የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ” አለ።
አንተን ለጥፋት፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ለማፍዋጫ እሰጥ ዘንድ የዘንበሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቃችኋል፥ በምክራቸውም ሄዳችኋል፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።