ኢሳይያስ 11:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጕድጓድና በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፤ ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጕድጓድ ይከትታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጡት የሚጠባ ሕፃን በአደገኛ እባብ ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፤ ጡት የጣለም ሕፃን እጁን በእፉኝት ጉድጓድ ይከትታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጡት የሚጠባው ሕፃን በእባብ ጒድጓድ አጠገብ ይጫወታል፤ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኚት ቤት ላይ እጁን ያኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚጠባውም ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፥ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል። |
እነርሱም አይጐዱትም፤ በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ ማንንም አይጐዱም፤ አያጠፉምም፤ ብዙ ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
ፍልስጥኤም ሆይ፥ ከእባቡ ዘር እፉኝት ይወጣልና፥ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና፥ የኀይላችሁ ቀንበር ተሰብሮአልና ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
የእባብን ዕንቍላል ቀፈቀፉ፤ የሸረሪትንም ድር አደሩ፤ እንቁላላቸውንም የሚበላ ሰው ፈጥኖ ይሞታል፤ እንቍላሉም ሲሰበር እባብ ይወጣል።