ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
ኢሳይያስ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ፥ ይህን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው? እንግዲህ አደባባዬን ደግማችሁ አትረግጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቴ ለመቅረብ ስትመጡ፣ ይህን ሁሉ እንድታመጡ፣ የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፊቴ ለመቅረብ ስትመጡ፤ ይህን ሁሉ እንድታመጡ፤ የመቅደሴን ደጅ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን ለመገናኘት እንድትመጡና የመቅደሴን አደባባይ እንድትረግጡ ማን ጠየቃችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ ይህን የመቅደሴን አደባባይ መርገጣችሁን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው? |
ከንቱን የሚናገር ይግባና ይይ፤ ልቡ በላዩ ላይ ኀጢአትን ሰበሰበ፤ ወደ ሜዳ ይወጣል ይናገራልም፥ በእኔም ላይ ይተባበራል።
ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤ የጠቢባንንም ትምህርት ለመስማት ቅረብ፤ ዳግመኛም ከሰነፎች ስጦታ መሥዋዕት አድርገህ ከመቀበል ተጠበቅ፤ እነርሱ መልካም ለመሥራት ዐዋቂዎች አይደሉምና።
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤