“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ሆሴዕ 8:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሕጎችን እጽፍለታለሁ፤ ነገር ግን ሥርዐቱና የተወደደው መሠዊያው እንደ እንግዳ ነገር ተቈጠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕጌ ውስጥ ያለውን ብዙውን ነገር ጻፍሁላቸው፤ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሺዎች የሚቆጠሩትን ሕጎቼን ጽፌለት እንኳ እንደ እንግዳ ነገር ተቆጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ለእነርሱ ከሕጌ ብዙ መመሪያዎችን ጽፌ ሰጠኋቸው፤ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሕጌን ብዛት ጽፌለታለሁ፥ እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጥረውታል። |
“ነገር ግን ተመልሰው ዐመፁብህ፤ ሕግህንም ወደ ኋላቸው ጣሉት፤ ወደ አንተም ይመለሱ ዘንድ የመሰከሩባቸውን ነቢያትህን ገደሉ፤ እጅግም አስቈጡህ።
ሕዝቤ አእምሮ እንደሌላቸው ይመስላሉ፤ አንተም አእምሮህ ተለይቶሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እተውሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።