ሆሴዕ 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቤም ከመኖሪያው ተነሥቶአል፤ እግዚአብሔርም በክብሩ ላይ ተቈጣ፤ ከፍ ከፍም አያደርገውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ማለትን መረጡ፤ ወደ ልዑል ቢጣሩም፣ በምንም ዐይነት አያከብራቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቤም ከእኔ ወደ ኋላ መመለስን በጽኑ ወደዱ፤ በአንድነትም ወደ ልዑሉ ይጣራሉ፥ እርሱ ግን ከፍ ከፍ አያደርጋቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ከእኔ መራቅን ፈለጉ፤ ይሁን እንጂ ለእርዳታ ወደ ላይ ይጮኻሉ፤ ግን ማንም ከችግራቸው አያወጣቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቤም ከእኔ ይመለሱ ዘንድ ወደዱ፥ ወደ ላይም ቢጠሩአቸው ማንም ከፍ ከፍ ያደርጋቸው ዘንድ አይችልም። |
በምድር ጽድቅን የማይማርና መልካምን የማያደርግ ኃጥእ አልቆአልና፥ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኀጢአተኛን ያስወግዱታል።
አቤቱ! ኀጢአታችን ብዙ ነውና፥ በአንተም ላይ ኀጢአት ሠርተናልና ኀጢአታችን ተቃውሞናል፤ ነገር ግን ስለ ስምህ ብለህ አድርግ።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
አባቶቻቸው ከግብፅ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፤ በቀንና በሌሊት ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባቸው ነበር፤ አዎ ልኬባቸዋለሁ።
ነገር ግን አንገታቸውን አደነደኑ እንጂ አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም፤ አባቶቻቸውም ከአደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
አሦር አያድነንም፤ በፈረስም ላይ አንቀመጥም፤ ድሃአደጉም በአንተ ዘንድ ይቅርታን ያገኛልና ከእንግዲህ ወዲህ የእጆቻችንን ሥራ አምላኮቻችን ናችሁ አንላቸውም።”
ወደ ከንቱ ነገር ተመለሱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ከምላሳቸው ስንፍና የተነሣ በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ይህም በግብፅ ምድር ውስጥ መሳለቂያ ይሆንባቸዋል።