ዕብራውያን 9:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጀመሪያዪቱም ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበረባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንኳን ተተክሎ ነበር፤ በመጀመሪያው ክፍል መቅረዙ፣ ጠረጴዛውና የመሥዋዕቱ ኅብስት ነበረበት፤ ይህም ስፍራ ቅድስት ይባላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳን ተዘጋጅቶ ነበር፥ በእርስዋም ውስጥ ቅድስት በምትባለው መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት ክፍሎች ያሉአት ድንኳን ተዘጋጅታ ነበር። መቅረዙና ጠረጴዛው፥ የመሥዋዕቱም ኅብስት የነበረባት መጀመሪያይቱ ክፍል “ቅድስት” ትባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመጀመሪያይቱ ድንኳን ተዘጋጅታ ነበርና፥ በእርስዋም ቅድስት በምትባለው ውስጥ መቅረዙና ጠረጴዛው የመስዋዕቱም ኅብስት ነበረባት፤ |
“መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት።
“ለድንኳኑም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ዐሥር መጋረጆችን ሥራ፤ ኪሩቤልም በእነርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብልሃት ትሠራቸዋለህ።
መጋረጃውንም በምሰሶዎች ላይ ስቀለው፤ በመጋረጃውም ውስጥ የምስክሩን ታቦት አግባው፤ መጋረጃውም በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ መካከል መለያ ይሁናችሁ።
ገበታውንም በመጋረጃው ውጭ፥ መቅረዙንም በገበታው ፊት ለፊት በድንኳኑ በደቡብ ወገን አድርግ፤ ገበታውንም በድንኳኑ በሰሜን ወገን አድርገው።
“እኔንም በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀድሳቸው ዘንድ የምታደርግላቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች ትወስዳለህ።