እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ናቸው፤ አባታቸውም ይህን ነገር ነገራቸው፤ ባረካቸውም፤ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸው።
ዕብራውያን 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ታላቁ ታናሹን እንደሚባርከው ያለ ጥርጥር ይታወቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትንሹ በትልቁ እንደሚባረክ ጥርጥር የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ ምንም ጥርጥር የሌለውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታናሹ ከታላቁ ቡራኬን እንደሚቀበል ጥርጥር የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትንሹንም በታላቁ እንዲባርክ ክርክር የሌለበት ነገር ነው። |
እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ናቸው፤ አባታቸውም ይህን ነገር ነገራቸው፤ ባረካቸውም፤ እያንዳንዳቸውንም እንደ በረከታቸው ባረካቸው።
ዳዊትም ቤተ ሰቡን ሊመርቅ ተመለሰ። የሳኦል ልጅ ሜልኮልም ዳዊትን ለመቀበል ወጣችና ሰላምታ ሰጠችው፥ “ከሚዘፍኑት አንዱ እንደሚገለጥ የእስራኤል ንጉሥ በአገልጋዮቹ ሚስቶች ፊት በመገለጡ ምንኛ የተከበረ ነው!” አለች።
ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምፃቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ ማደሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።
እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።