ዕብራውያን 3:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛሬ ቃሉን ብትሰሙ እነዚያ እንደ አሳዘኑት ጊዜ ልባችሁን አታጽኑ” ብሎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” እንደተባለው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ በዚያ በዐመፃው ጊዜ እንዳደረጋችሁት ዐይነት ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ” ተብሎ እንደ ተነገረው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየተባለ፦ ዛሬ ድምጹን ብትሰሙት፥ በማስመረር እንደሆነ ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ። |
የእግዚአብሔርን ልጅ የከዳ፥ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኩስ ነገር የቈጠረ፥ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?
“ዛሬ ቃሉን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” በፊት እንደ ተባለ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር፥ “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀጥራል።