Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 4:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 “ዛሬ ቃሉን ብት​ሰ​ሙት ልባ​ች​ሁን እል​ከኛ አታ​ድ​ርጉ፤” በፊት እንደ ተባለ ይህን ከሚ​ያ​ህል ዘመን በኋላ በዳ​ዊት ሲና​ገር፥ “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀ​ጥ​ራል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ዛሬ” ብሎ እንደ ገና አንድን ቀን ወሰነ፤ ይህም ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት በኩል፣ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣ ልባችሁን አታደንድኑ” ተብሎ ቀደም ሲል እንደ ተነገረው ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ይህም አስቀድሞ እንደተባለው፥ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” በፊት እንደተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደገና ይቀጥራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ይህም አስቀድሞ እንደተባለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ፥ ልባችሁን እምቢተኛ አታድርጉ።” ሲል እግዚአብሔር ከብዙ ዘመን በኋላ በዳዊት አማካይነት በተናገረው ቃል “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ቀን በመወሰኑ ተረጋግጦአል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በፊት እንደ ተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር፦ ዛሬ ብሎ አንድ ቀን እንደ ገና ይቀጥራል።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 4:7
12 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማ​ንያ አራት ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎ​ሞን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በነ​ገሠ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚ​ባ​ለው በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት መሥ​ራት ጀመረ።


የአ​ሕ​ዛብ ወገ​ኖች፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፤


እርሱም “እንኪያስ ዳዊት ‘ጌታ ጌታዬን “ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ፤” አለው፤’ ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል?


ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ‘ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው አለ።’


እርሱ ራሱ ዳዊት በመ​ዝ​ሙር መጽ​ሐፍ ‘ጌታ ጌታ​ዬን በቀኜ ተቀ​መጥ፥


“እና​ንተ ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስለ አባ​ቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀ​በ​ረም፥ መቃ​ብ​ሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ትፈ​ቅ​ዱ​ል​ኛ​ላ​ች​ሁን?


ክር​ስ​ቶስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ እን​ደ​ሚ​ነሣ፥ ሥጋ​ዉም በመ​ቃ​ብር እን​ደ​ማ​ይ​ቀር፥ ጥፋ​ት​ንም እን​ደ​ማ​ያይ አስ​ቀ​ድሞ ዐውቆ ተና​ገረ።


እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ባል​ተ​ስ​ማሙ ጊዜ ጳው​ሎስ አን​ዲት ቃል ከተ​ና​ገረ በኋላ ከእ​ርሱ ተመ​ለሱ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱስ በነ​ቢዩ በኢ​ሳ​ይ​ያስ አን​ደ​በት ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን በእ​ው​ነት እን​ዲህ ብሎ መል​ካም ነገር ተና​ግ​ሮ​አል።


“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ እነ​ዚያ እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ” ብሎ​አ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos