ስለ እርሱ የምንናገርለትን የሚመጣውን ዓለም ለመላእክት ያስገዛ አይደለም።
ይህን የምንናገርለትን መጪውን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም።
ስለ እርሱ የምንናገርለት፥ የሚመጣውን ዓለም ያስገዛው ለመላእክት አይደለምና።
እግዚአብሔር ወደ ፊት የሚመጣውን፥ ይህን የምንነጋገርበትን ዓለም ለመላእክት አላስገዛም
ስለ እርሱ የምንናገርበትን የሚመጣውን ዓለም ለመላእክት ያስገዛው አይደለምና።
ለአሕዛብም ሁሉ ምስክር እንዲሆን ይህ የመንግሥት ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል፤ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።
በዚህ የሚኖር ከተማ ያለን አይደለም፤ የምትመጣውን እንሻለን እንጂ።
መልካሙን የእግዚአብሔርን ቃል፥ የሚመጣውንም የዓለምን ኀይል የቀመሱትን፥
ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን።
ሰባተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል፤”