Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 መል​ካ​ሙን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል፥ የሚ​መ​ጣ​ው​ንም የዓ​ለ​ምን ኀይል የቀ​መ​ሱ​ትን፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኀይል የቀመሱትን፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና መጪውንም የዓለም ኃይል የቀመሱ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የእግዚአብሔርን መልካም ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኀይል ቀምሰው ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 6:5
13 Referencias Cruzadas  

በጭ​ን​ጫም ላይ የወ​ደ​ቀው ሰም​ተው ነገ​ሩን በደ​ስታ የሚ​ቀ​በ​ሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊ​ዜው ያም​ናሉ እንጂ ሥር የላ​ቸ​ውም፤ መከ​ራም በአ​ገ​ኛ​ቸው ጊዜ ይክ​ዳሉ።


በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዕውቀት ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ ዳግመኛ በእርስዋ ተጠላልፈው የተሸነፉ ቢሆኑ፥ ከፊተኛው ኑሮአቸው ይልቅ የኋለኛው የባሰ ሆኖባቸዋል።


ስለ እርሱ የም​ን​ና​ገ​ር​ለ​ትን የሚ​መ​ጣ​ውን ዓለም ለመ​ላ​እ​ክት ያስ​ገዛ አይ​ደ​ለም።


ሄሮድስ ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው እንደ ሆነ አውቆ ይፈራውና ይጠባበቀው ነበር፤ እርሱንም ሰምቶ በብዙ ነገር ያመነታ ነበር፤ በደስታም ይሰማው ነበር።


ያላ​ወ​ቋት ወጥ​መድ ትም​ጣ​ባ​ቸው፥ የሸ​ሸ​ጓ​ትም ወጥ​መድ ትያ​ዛ​ቸው፤ በዚ​ህ​ችም ወጥ​መድ ውስጥ ይው​ደቁ።


በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።


የመ​ዳ​ን​ንም የራስ ቍር በራ​ሳ​ችሁ ላይ ጫኑ፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ሰይፍ ያዙ፤ ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚ​ሠ​ራም ሁለት ልሳን ካለው ሰይ​ፍም ሁሉ ይልቅ የተ​ሳለ ነው፤ ነፍ​ስ​ንና መን​ፈ​ስ​ንም፥ ጅማ​ት​ንና ቅል​ጥ​ም​ንም እስ​ኪ​ለይ ድረስ ይወ​ጋል፤ የል​ብ​ንም ስሜ​ትና አሳብ ይመ​ረ​ም​ራል።


ዓለም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ተፈ​ጠረ፥ የሚ​ታ​የ​ውም ነገር ከማ​ይ​ታ​የው እንደ ሆነ በእ​ም​ነት እና​ው​ቃ​ለን።


የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል።” በወንጌልም የተሰበከላችሁ ቃል ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios