አዳምንም አስወጣው፤ ደስታ በሚገኝባት በገነት አንጻርም አኖረው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በእጃቸው የያዙ ኪሩቤልን አዘዛቸው።
ዕብራውያን 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ መላእክቱም፥ “መላእክቱን ነፋሳት፥ የሚላኩትንም የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው እርሱ ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ መላእክትም ሲናገር፣ “መላእክቱን ነፋሳት፣ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ መላእክትም “መላእክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ” ይላል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ መላእክቱ ግን “መላእክቱን መናፍስት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ መላእክትም፦ መላእክቱን መናፍስት አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ |
አዳምንም አስወጣው፤ ደስታ በሚገኝባት በገነት አንጻርም አኖረው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በእጃቸው የያዙ ኪሩቤልን አዘዛቸው።
ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በሁለቱ መካከል ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ንውጽውጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።
ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለቱ ክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው እግሮቻቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው ይበርሩ ነበር።
መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?