Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ሱራ​ፌ​ልም በዙ​ሪ​ያው ቆመው ነበር፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ስድ​ስት ክንፍ ነበ​ረው፤ በሁ​ለቱ ክን​ፎ​ቻ​ቸው ፊታ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይሸ​ፍኑ ነበር፤ በሁ​ለ​ቱም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ይበ​ርሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሱራፌልም ከርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበርሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ እያንዳንዳቸውም ስድስት ክንፍ ነበራቸው። በሁለት ክንፍ ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለት ክንፍ እግራቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፍ ይበሩ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ሱራፌል ተብለው የሚጠሩ መላእክትም በዙሪያው ነበሩ፤ እያንዳንዱ መልአክ ስድስት ክንፍ አለው፤ በሁለቱ ክንፎቹ ፊቱን ይሸፍናል፤ በሁለቱ ክንፎቹ እግሮቹን ሸፍኖ በሁለት ክንፎቹ ይበር ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፥ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 6:2
34 Referencias Cruzadas  

አብ​ራ​ምም በግ​ን​ባሩ ወደቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን እን​ዲህ አለው፦


ኤል​ያ​ስም ያን በሰማ ጊዜ ፊቱን በመ​ጐ​ና​ጸ​ፊ​ያው ሸፈነ፤ ወጥ​ቶም በዋ​ሻው ደጃፍ ቆመ። እነ​ሆም፥ “ኤል​ያስ ሆይ፥ ወደ​ዚህ ለምን መጣህ?” የሚል ቃል ወደ እርሱ መጣ።


ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል የሰ​ማ​ሁት እኔ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው ቆመው አየሁ።


የኪ​ሩ​ብም አን​ደ​ኛው ክንፍ አም​ስት ክንድ፥ የኪ​ሩ​ብም ሁለ​ተ​ኛው ክንፍ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ ከአ​ን​ደ​ኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስከ ሁለ​ተ​ኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ ዐሥር ክንድ ነበረ።


ሁለ​ቱም ኪሩ​ቤል በው​ስ​ጠ​ኛው ቤት መካ​ከል ነበሩ። የኪ​ሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸው ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ የአ​ን​ዱም ኪሩብ ክንፍ አን​ደ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ኪሩብ ክንፍ ሁለ​ተ​ኛ​ውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁ​ለ​ቱም ክን​ፎች በቤቱ መካ​ከል እርስ በር​ሳ​ቸው ይነ​ካኩ ነበር።


ኪሩ​ቤ​ልም በታ​ቦቷ ስፍራ ላይ ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ታቦቷ​ንና የተ​ቀ​ደሱ ዕቃ​ዎ​ችን በስ​ተ​ላይ በኩል ሸፍ​ነው ነበር።


ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ።


ከዕ​ለ​ታት አንድ ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ቆም መጡ፤ ሰይ​ጣ​ንም ደግሞ ከእ​ነ​ርሱ ጋር መጣ።


እነሆ፥ በቅ​ዱ​ሳኑ እንኳ አይ​ታ​መ​ንም፤ ሰማ​ይም በፊቱ ንጹሕ አይ​ደ​ለም።


እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም አይ​ተ​ማ​መ​ና​ቸ​ውም፥ መላ​እ​ክ​ቱ​ንም በጭ​ንቅ ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ቸ​ዋል።


ጨለ​ማን ታመ​ጣ​ለህ ሌሊ​ትም ይሆ​ናል፤ በእ​ር​ሱም የዱር አራ​ዊት ሁሉ ይወ​ጡ​በ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ልግ ልብ ደስ ይበ​ለው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ትጸ​ና​ላ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊዜ ፊቱን ፈልጉ።


ከወ​ር​ቅና ከክ​ቡር ዕንቍ ይልቅ ይወ​ደ​ዳል፤ ከማ​ርና ከማር ወለ​ላም ይልቅ ይጣ​ፍ​ጣል።


እኛ በቍ​ጣህ አል​ቀ​ና​ልና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም ደን​ግ​ጠ​ና​ልና።


ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ይሸ​ፍ​ናሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እርስ በርሱ ይተ​ያ​ያል፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ ስር​የት መክ​ደ​ኛው ይሁን።


ደግ​ሞም፥ “እኔ የአ​ባ​ቶ​ችህ አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ ዘንድ ፈር​ቶ​አ​ልና ፊቱን መለሰ።


ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ የዘ​ረጉ ሆኑ፥ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ሸፈኑ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተያዩ፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ መክ​ደ​ኛው ተመ​ለ​ከቱ።


ከሱ​ራ​ፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፤ በእ​ጁም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በጕ​ጠት የወ​ሰ​ደው ፍም ነበረ።


ክን​ፋ​ቸ​ውም በላይ ተዘ​ር​ግቶ ነበር፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሁለት ሁለት ክን​ፋ​ቸው የተ​ያ​ያዙ ነበሩ፤ ሁለት ሁለ​ቱም ገላ​ቸ​ውን ይከ​ድኑ ነበር።


ሲሄ​ዱም የክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ድምፅ እንደ ብዙ ውኃ ድምፅ፥ ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል የአ​ም​ላ​ክም ድምፅ፥ እንደ ታላቅ ሠራ​ዊ​ትም ድምፅ ሆኖ ሰማሁ፤ ሲቆ​ሙም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ይሰ​በ​ስቡ ነበር።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከሰ​ሜን በኩል ዐውሎ ነፋ​ስና ታላቅ ደመና፥ የሚ​በ​ር​ቅም እሳት መጣ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ፀዳል ነበረ፤ በመ​ካ​ከ​ልም በእ​ሳቱ ውስጥ የሚ​ብ​ለ​ጨ​ለጭ ነገር ነበረ።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ፊት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ክንፍ ነበ​ሩት።


የሁ​ሉም ክን​ፎ​ቻ​ቸው አንዱ ከአ​ንዱ ጋር የተ​ያ​ያዘ ነው፤ ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ ሳይሉ አቅ​ን​ተው ይሄ​ዳሉ፤ አን​ዱም አን​ዱም ወደ​ፊቱ ይሄ​ዳል።


ኪሩ​ቤ​ልም ሲሄዱ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተያ​ይ​ዘው ይሄዱ ነበር፤ ኪሩ​ቤ​ልም ይበሩ ዘንድ ክን​ፋ​ቸ​ውን ከም​ድር በሚ​ያ​ነሡ ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የተ​ያ​ያዘ መን​ኰ​ራ​ኵ​ራ​ቸው አይ​መ​ለ​ስም ነበር።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት አራት ፊት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ክንፍ ነበ​ሩት፤ የሰ​ውም እጅ አም​ሳያ ከክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው በታች ነበረ።


እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው።


ዕጣን በሚ​ያ​ጥ​ን​በት ጊዜም ሕዝቡ በሙሉ በውጭ ይጸ​ልዩ ነበር።


ስለ መላ​እ​ክ​ቱም፥ “መላ​እ​ክ​ቱን ነፋ​ሳት፥ የሚ​ላ​ኩ​ት​ንም የእ​ሳት ነበ​ል​ባል የሚ​ያ​ደ​ር​ጋ​ቸው እርሱ ነው” አለ።


በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ መካከል ሲበር አየሁ፤


አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።


መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑና በሽማግሌዎቹ በአራቱም እንስሶቹ ዙሪያ ቆመው ነበር፤ በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ ለእግዚአብሔርም እየሰገዱ


አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” ሲል ሰማሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos