ዕንባቆም 2:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተረትም አይተርቱበትምን? የሚነክሱህ ድንገት አይነሡብህምን? የሚያስጨንቁህም ይነቃሉ፣ ለእነርሱም ብዝበዛ ትሆናለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባለዕዳ ያደረግሃቸው ድንገት አይነሡብህምን? ነቅተውስ አያስደነግጡህምን? በእጃቸውም ትወድቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበዳሪዎችህ ድንገት አይነሡምን? የሚያንቀጠቅጡህ አይነቁምን? ለእነርሱም ብዝበዛ ትሆናለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ ዕዳዎቻችሁ በድንገት አይነሡምን? ተነሥተውስ አያርበደብዱአችሁምን? ከዚያ በኋላ እናንተ የእነርሱ ምርኮኞች ትሆናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተረትም አይተርቱበትምን? የሚነክሱህ ድንገት አይነሡብህምን? የሚያስጨንቁህም ይነቃሉ፥ ለእነርሱም ብዝበዛ ትሆናለህ። |
የኤፍሬምም ቅናት ይሻራል፤ የይሁዳም ጠላቶች ይጠፋሉ፤ ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፤ ይሁዳም ኤፍሬምን አያስጨንቅም።
ከሰሜንና ከፀሐይ መውጫ የሚመጡትን አስነሣሁ፤ በስሜም ይጠራሉ፤ አለቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እንደሚረግጥ ሸክላ ሠሪ እንዲሁ ይረግጡአቸዋል።
ከምሥራቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከርሁት ምክር ዎፍን እጠራለሁ፤ ተናገርሁ፤ አመጣሁም፤ ፈጠርሁ፤ አደረግሁም፤ አመጣሁት፤ መንገዱንም አቀናሁለት።
ስለዚህ ምክንያት ጥፋት ይመጣብሻል፤ ጥልቀቱን አታውቂም፤ በውስጡም ትወድቂያለሽ፤ ጕስቁልና ይመጣብሻል፤ ማምለጥም አይቻልሽም፤ ሞት ድንገት ይመጣብሻል፤ አታውቂምም።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋንም፥ አለቆችዋንና ሹሞችዋን፥ ኀያላኖችዋንም አሰክራለሁ፤ ለዘለዓለምም አንቀላፍተው አይነቁም ይላል ስሙ ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
እነሆ አስማት የማይከለክላቸውን የሚገድሉ እባቦችን እሰድድባችኋለሁ፤ እነርሱም ይነድፉአችኋል፥” ይላል እግዚአብሔር።