እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ዘፍጥረት 7:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ የነበረውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ፥ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፥ እስከ ሰማይ ወፍም ድረስ ተደመሰሰ፤ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፉ፤ ሰዎችና እንስሳት በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች ከምድር ላይ ጠፉ፤ ኖኅና ከርሱ ጋራ በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ሕያው ፍጥረት ሁሉ፥ ሰዎችንም፥ እንስሶችንም፥ ወፎችንም፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፋ። ከሞት የተረፉት ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በምድር ላይ ያለውን ሕያው ፍጥረት ሁሉ፥ ሰዎችንም፥ እንስሶችንም፥ ወፎችንም፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች ሳይቀሩ ሁሉንም አጠፋ። ከሞት የተረፉት ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩት ብቻ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ የነበውም ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ፤ እስከሚርመሰመሰውም ሁሉ ድረስ፤ እስከ ሰማይ ወፍ ድረስ ተደመሰሰ ከምድርም ተደመሰሱ። ኖኅም አብረውት በመርከብ ከነበሩት ጋር ብቻውን ቀረ። |
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
ኖኅም ስለማይታየው ነገር የነገሩትን ባመነ ጊዜ ፈራ፤ ቤተ ሰቡንም ያድን ዘንድ ክፍል ያላት መርከብን ሠራ፤ በዚህም ዓለምን አስፈረደበት፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
ጌታ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን ከፈተና እንዴት እንዲያድን በደለኞችንም ይልቁንም በርኵስ ምኞት የሥጋን ፍትወት እየተከተሉ የሚመላለሱትን ጌትነትንም የሚንቁትን እየቀጣቸው ለፍርድ ቀን እንዴት እንዲጠብቅ ያውቃል። ደፋሮችና ኵሩዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን ሲሳደቡ አይንቀጠቀጡም፤