ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ።
ዘፍጥረት 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ስባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነም እንስሳ ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት ውሰድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጹሕ ከሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ሰባት ወንድ፥ ሰባት ሴት ከአንተ ጋር ወደ መርከቡ አስገባ፤ ንጹሕ ካልሆኑት ወንዶችና ሴቶች እንስሶች ሁሉ ግን፥ አንድ ወንድ አንድ ሴት አስገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንጹሕ እንስሳ ሁሉ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት ንጽሕ ካልሆነ እንስሳም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት፤ |
ከንጹሕ የሰማይ ወፍ ደግሞ ሰባት ሰባት ተባትና እንስት፥ ንጹሕ ካልሆነ የሰማይ ወፍም ሁለት ሁለት ተባትና እንስት እያደረግህ በምድር ላይ ለምግብና ለዘር ይቀር ዘንድ ለአንተ ትወስዳለህ።
ከንጹሓን ወፎችና ንጹሓን ካልሆኑ ወፎች፥ ከንጹሕ እንስሳ፥ ንጹሕም ካልሆነው እንስሳ፥ በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሰው ሁሉ፥
ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠውያዉን ሠራ፥ ከንጹሕም እንስሳ ሁሉ፥ ከንጹሓን ወፎችም ሁሉ ወሰደ፤ በመሠውያውም ላይ መሥዋዕትን አቀረበ።
በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፤ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው።