እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ዘፍጥረት 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰባት ቀን በኋላም የጥፋት ውኃ በምድር ላይ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰባት ቀንም በኋላ የጥፋት ውኃ በምድር ላይ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሰባትም ቀን በኋላ የጥፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰባት ቀንም በኍላ የጥፋት ውኂ በምድር ላይ ሆነ። |
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና፤ የፈጠርሁትንም ፍጥረት ሁሉ ከምድር ሁሉ ላይ አጠፋለሁና።”
ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ ሲበሉና ሲጠጡ፥ ሲያገቡና ሲጋቡ ነበረ፤ የጥፋት ውኃም መጥቶ ሁሉን አንድ አድርጎ አጠፋ።