የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።
ዘፍጥረት 50:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰረገሎችም፥ ፈረሰኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ፤ ሠራዊቱም ብዙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ሠረገሎችና ፈረሰኞች ዐብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰረጎሎችም ፈረሰኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ፥ ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከትለውት ወጡ፤ በጠቅላላው የተከተለው አጀብ እጅግ ብዙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰረጎሎችም ፈረሶኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ ሠራዎቱም እጅግ ብዙ ነበረ። |
የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፤ ስገዱ እያለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እንዲሄድ አደረገ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።
ዮሴፍም ሰረገላውን አዘጋጀ፤ አባቱንም እስራኤልን ሊገናኘው ወደ ኤሮስ ከተማ ወጣ፤ በአየውም ጊዜ አንገቱን አቀፈው፤ ረዥም ጊዜም አለቀሰ።
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
የዮሴፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም፥ የአባቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን፥ ከብቶቻቸውንም ብቻ በጌሤም ተዉ።
ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሶች በግብፅ ስትታመን፥ ከጌታዬ አገልጋዮች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትመልስ ዘንድ እንዴት ይቻልሃል?
እነሆም፥ እኔ የፈርዖንንና የግብፃውያንን ልብ አጸናለሁ፤ በኋላቸውም ይገባሉ፤ በፈርዖንና በሠራዊቱም ሁሉ፥ በሰረገሎቹም፥ በፈረሰኞቹም ላይ እከብራለሁ።
ውኃውም ተመልሶ በኋላቸው ወደ ባሕር የገቡትን ሰረገሎችን፥ ፈረሰኞችንም፥ የፈርዖንንም ሠራዊት ሁሉ ከደነ፤ ከመጡትም ሁሉ አንድ ስንኳ የቀረ የለም።