ዘፍጥረት 49:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዳን ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ በወገኑ ይፈርዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዳን፣ ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ፣ በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳን በወገኑ ይፈርዳል፥ ከእስራኤል ነገድ እንደ አንዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዳን፥ ከእስራኤል ነገዶች አንዱ ለሆነው ሕዝብ ፈራጅ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳም በወገኑ ይፈርዳል ከእስርኤል ነገስ እንደ አንዱ |
ዕረፍትም መልካም መሆንዋን፥ ምድሪቱም የለማች መሆንዋን በአየ ጊዜ ምድርን ያርሳት ዘንድ ትከሻውን ዝቅ አደረገ፤ በሥራም ገበሬ ሆነ።
ዳን በጎዳና ላይ እንደሚያደባ እባብ ይሆናል፤ በመንገዱም የፈረሱን ሰኰና እንደሚናደፍ እንደ ቀንዳም እባብ ነው፤ ፈረሰኛውም ወደኋላው ይወድቃል።
ከሠራዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊታቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የአሚሳዲ ልጅ አኪያዜር አለቃ ነበረ።