አህያይቱን በወይን ግንድ ያስራል፤ የአህያይቱንም ግልገል በወይን ሐረግ፤ ልብሱን በወይን ያጥባል፤ መጐናጸፊያውንም በዘለላው ደም።
ዘፍጥረት 49:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኖቹ ከወይን ይልቅ ደስ ያሰኛሉ፤ ጥርሱም ከወተት ይልቅ ነጭ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኑም ከወይን ይቀላል፥ ጥርሱም ከወተት ይነጻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይኖቹ ከወይን ጠጅ ይልቅ ይቀላሉ፤ ጥርሶቹ ከወተት ይልቅ ይነጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኑም ከወይን ይቀላል፤ ጥርሱም ከወተት ነጭ ይሆናል። |
አህያይቱን በወይን ግንድ ያስራል፤ የአህያይቱንም ግልገል በወይን ሐረግ፤ ልብሱን በወይን ያጥባል፤ መጐናጸፊያውንም በዘለላው ደም።