ከዚህም ነገር በኋላ እንዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባታችን ደከመ” ብለው ለዮሴፍ ነገሩት፤ እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።
ዘፍጥረት 48:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለያዕቆብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፤ እስራኤልም ተጠነካከረ፤ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለያዕቆብ፣ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቷል” ተብሎ በተነገረው ጊዜ፣ እስራኤል ተበረታትቶ ዐልጋው ላይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለያዕቆብም፦ “እነሆ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፥ እስራኤልም ሰውነቱን አበረታቶ፥ በአልጋው ላይ ተቀመጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ልጁ ዮሴፍ ሊጐበኘው መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሰውነቱን አበረታቶ በመኝታው ላይ ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለያዕቆብም፦ እነሆ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል ብለው ነገሩች እስራኤልም ተጠነካከረ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ። |
ከዚህም ነገር በኋላ እንዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባታችን ደከመ” ብለው ለዮሴፍ ነገሩት፤ እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።
የአምላኬም እጅ በእኔ ላይ መልካም እንደ ሆነች፥ ንጉሡም የነገረኝን ቃል ነገርኋቸው። “ተነሡ እንሥራ” አልኋቸው። እጆቻቸውንም ለበጎ ሥራ አበረቱ።
ኢያሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሻገራልና፥ አንተም የምታያትን ምድር እርሱ ያወርሳቸዋልና ኢያሱን እዘዘው፤ አደፋፍረውም፥ አጽናውም።