በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን የጥጋብ ዓመታት እህል ሁሉ ሰበሰበ፤ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱም ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ።
ዘፍጥረት 47:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቡንም ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ አንሥቶ እስከ ሌላው ዳርቻዋ ድረስ አገልጋዮች አደረጋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም የግብጽን ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር የፈርዖን ገባር አደረገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡንም ሁሉ ከግብጽ ዳርቻ አንሥቶ እስከ ሌላው ዳርቻዋ ድረስ ባርያዎች አደረጋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ በግብጽ አገር ዳር እስከ ዳር ያሉት ሰዎች ሁሉ የንጉሡ ባሪያዎች እንዲሆኑ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡንም ሁሉ ከግብፅ ዳርቻ አንሥቶ እስከ ሌላው ዳርቻዋ ድረስ ባርያዎች አደረጋቸው። |
በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን የጥጋብ ዓመታት እህል ሁሉ ሰበሰበ፤ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱም ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ።
ዮሴፍም የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛ፤ የግብፅ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለጸናባቸው ርስታቸውን ሸጠዋልና፤ ምድሪቱ ለፈርዖን ሆነች።
ዮሴፍ የካህናትን ምድር ብቻ አልገዛም፤ ፈርዖን ለካህናቱ ድርጎ ይሰጣቸው ነበርና፥ ፈርዖንም የሰጣቸውን ድርጎ ይበሉ ነበር፤ ስለዚህም ምድራቸውን አልሸጡም።